Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline26 Dec 2024, 5:15 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Wood And Wood Working

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ እና ለመሰብሰቢያ አዳራሽ አገልግሎት የሚውል ወንበርና ጠረጴዛ ዕቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር  ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/10/2017

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ እና ለመሰብሰቢያ አዳራሽ አገልግሎት የሚውል ወንበርና ጠረጴዛ ዕቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ፤ የቫት እና ቲን ተመዝጋቢ ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ/ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።   

ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ  (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ስልክ ቁጥር :- 011470-90-95 ወይም 011442-36-08

ፋክስ:-0114-421312

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

በኢትዮጵያ  ኢንቨስትመንት  ሆልዲንግስ  የኢትዮጵያ  የግብርና  ሥራዎች  ኮርፖሬሽን

Save Tender