የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል በሎት 1 የገልባጭ መኪናዎችን ከነሎደሩ፣ በሎት 2 ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር እና ሮለር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየትና በሎት 3 ለድልድይ ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚሆኑ ሲምንቶና ፌሮ ብረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
South West Ethiopia Roads Authority (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2017
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል በሎት 1 የገልባጭ መኪናዎችን ከነሎደሩ፣ በሎት 2 ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር እና ሮለር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየትና በሎት 3 ለድልድይ ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚሆኑ ሲምንቶና ፌሮ ብረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን ይጋብዛል፦
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴከኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ “ኦርጅናል” እና “ኮፒ” በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም ለእያንዳንዱ ሎት በተለያየ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 በማስገባት የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታው ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሎት 1 እና ሎት 2 የጠቅላላ ዋጋ 1% እና ለሎት 3 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) በየሎት ለይተው ከጨረታ ሰነዳቸው ።ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፤ ከጨረታ ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች ለሎት 1 እና ሎት 2 ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግስት መ/ቤት ቢያንስ ሁለት የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
* ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ኢትዮጵያ
