የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የጂምናስቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ፣ የገቢ ምንጮቹን ለማስፋት እና ዘላቂ የግል ዘርፍ አጋርነቶችን ለመፍጠር የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ፣ የድርጅት አጋሮችን ቁጥር ማሳደግ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም ብቁ የማርኬቲንግ/ስፖንሰርሺፕ አፈላላጊ ኤጀንሲ ወይም አገልግሎት ሰጪ እንዲወዳደር ይጋብዛል።
የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: 001/2019
የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የጂምናስቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ፣ የገቢ ምንጮቹን ለማስፋት እና ዘላቂ የግል ዘርፍ አጋርነቶችን ለመፍጠር የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ፣ የድርጅት አጋሮችን ቁጥር ማሳደግ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም ብቁ የማርኬቲንግ/ስፖንሰርሺፕ አፈላላጊ ኤጀንሲ ወይም አገልግሎት ሰጪ እንዲወዳደር ይጋብዛል። የፌዴሬሽኑን የአሁኑን የግብይት ሁኔታ፣ ውድድሮችና የአጋርነት እድሎች መገምገም፣ የስፖንሰርሺፕ ስትራቴጂ፣ የዋጋ ደረጃዎች፣ የስፖንሰር ጥቅል እና የዓመት የግብይት እቅድ ማዘጋጀት፣ የሚመለከታቸውን ድርጅቶች መለየት፣ ድርድርን መደገፍ እና የስፖንሰር ግንኙነትን ማስተዳደር፣ በየሩብ ዓመቱ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የቀረቡ ሀሳቦች፣ ገቢ የተደረገ ገንዘብ እና የተፈጸሙ ግዴታዎች ሪፖርት ማቅረብ።
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- በሕጋዊ ሁኔታ የተመዘገበ ድርጅት መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተገቢ የንግድ ፈቃድና የግብር ምዝገባ ማቅረብ የሚችል፣
- ለፌዴሬሽኑ የሚያስገባውን ገቢ ጠቅሶ ማስገባት የሚችል፣ እያንዳንዱ ተጫራች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ በፌዴሬሽኑ ስም ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ካሸነፈ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በፌዴሬሽኑ አካውንት ማስያዣ ቅድሚያ ገቢ ማድረግ አለበት።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ስድስት ኪሎ በሚገኘው ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር 4ኛ ፎቅ በጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ፌዴሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ማስያዝ እና የሚጠየቀውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ጨረታውን ካሸነፈ 200,000 ብር ማስያዝ የሚችል ማንኛውም ተጫራች መጫረት ይችላል።
ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትንና ተያያዥ ሰነዶችን እና የገዙትን ሰነድ ኮፒ በሙሉ አያይዘው እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ።
የጨረታው መወዳደርያ ቀን ገደብ፣ ጨረታው ከወጣ በኋላ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር: 0911-46-80-91 / 0973-19-99-91 ወይም 0910-36-86-80 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን
✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Gymnastics Federation seeks a qualified marketing/sponsorship agency to grow the sport, expand revenue, and build private-sector partnerships—covering strategy, pricing, sponsor packages, outreach, negotiation, and quarterly reporting. Bidders must be legally registered with valid trade license and tax registration.
