Tender Detail

Tender Details

  • Company ገርጂ ጊዮርጊስ የገበያ ሱቆች አክሲዮን ማህበር
  • Address ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት ጀርባ በጊዮርጊስ ቤተከርስትያን መታጠፊያ መንገድ ላይ ገርጂ ጊዮርጊስ የገበያ ሱቆች አክሲዮን ማህበር ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 316 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912 20 52 95
  • Website
  • Deadline28 Nov 2024, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

ገርጂ ጊዮርጊስ የገበያ ሱቆች አክሲዮን ማህበር ባሰራው ህንፃ ውስጥ ያሉትን ሱቆችና ቢሮዎች በጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ገርጂ ጊዮርጊስ የገበያ ሱቆች አክሲዮን ማህበር


የጨረታ ማስታወቂያ

ገርጂ ጊዮርጊስ የገበያ ሱቆች አክሲዮን ማህበር ባሰራው ህንፃ ውስጥ ያሉትን ሱቆችና ቢሮዎች በጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም  ተጫራቾች  ከዚህ  በታች  የተዘረዘሩትን  መስፈርቶች  በማሟላት  ቀርበው  መወዳደር  ይችላሉ::

  1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ኦርጅናልና ኮፒ ይዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል ፡፡ በውክልና ሰነድ ለመግዛት ከፈለጉ የውከልና ማስረጃ ይዞ በአካል መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ለጨረታ የቀረቡ ሱቆችና ቢሮዎች የሚገኙት ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት ጀርባ በጊዮርጊስ ቤተከርስትያን መታጠፊያ መንገድ ላይ ነው፡፡
  3. ተጫራቾች ገርጂ ጊዮርጊስ የገበያ ሱቆች አክሲዮን ማህበር ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 316 በመምጣት ለኪራይ የተዘጋጁ ሱቅና ቢሮዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር / ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ ፡፡
  4. ለጨረታ የቀረቡት ሱቆችና ቢሮዎች የአንድ ካሬ ሜትር መነሻ ዋጋ በሰነዱ ላይ ተመልከቷል፡፡
  5. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 6፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሱቅ ወይም ቢሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የ10,000.00 / አስር ሺህ ብር / ሲፒኦ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 15 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የካሬ ሜትር ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡ በመቀጠል አሸናፊዎች ተለይተው የስም ዝርዝራቸው ይለጠፋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ሱቅ ወይም ቢሮ የአንድ ወር ቅድሚያ ከፍያ በመክፈል ውል በመፈራረም ይረከባል፡፡
  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912 20 52 95 ወይም 0911 31 73 80 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  10. የአክሲዮን ማህበሩ ጨረታውን የማጽደቅ ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ገርጂ ጊዮርጊስ የገበያ ሱቆች አክሲዮን ማህበር

Save Tender