በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት አመት ለክ/ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት አመት ለክ/ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት /መረጃዎች በማቅረብ/በጨረታ እንዲሳተፍ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- የአቅራቢ ስም ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ተመዝጋቢ የሆነ ፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል
- ተጫራቾች የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ) ብር በ ገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ) ልከ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማገ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም ፡፡ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10 % በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ(CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
- የመንግስትን የፋይናንስ ህግ እና መመሪያን የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መሰረት የተጫረተበት ዕቃ ናሙና “Sample” ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114450182 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
የሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
