Tender Detail

Tender Details

  • Deadline27 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Machinery

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የበቆሎ መፈልፈያ ኮምባይን ሀርቨስተር እና ሽለር ማሽን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።


በድጋሚ  የወጣ  የጨረታ  ማስታወቂያ

ብሔራዊ  ግልፅ  የጨረታ  ቁጥር : ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/02/2017

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የበቆሎ መፈልፈያ ኮምባይን ሀርቨስተር እና ሽለር ማሽን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ጨረታውን ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ ቁጥር 100057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ

ካሳንቺስ ከመናኸሪያ ሆቴል ወደ አቧሬ አቅጣጫ በሚወስደው አስፋልት

መንገድ ከጨርጨር ስጋ ቤት ዝቅ በማለት

የቀድሞው ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ

ስልክ ቁጥር 0115 58 67 25

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
  3. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው።
  4. ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-62-25 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ

Save Tender