የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2017 በጀት አመት ሎት:- 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2፡- የደንብ ልብስ፣ ሎት 3፡- ፕላንት ማሽነሪና መሳሪያዎች፣ ሎት 4፡- የህንጻ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች መግዣ፣ ሎት 5፡- ፕላንትና ማሸነሪ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
FEDERAL TAX APPEAL COMMISSION (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2017 በጀት አመት ሎት:- 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2፡- የደንብ ልብስ፣ ሎት 3፡- ፕላንት ማሽነሪና መሳሪያዎች፣ ሎት 4፡- የህንጻ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች መግዣ፣ ሎት 5፡- ፕላንትና ማሸነሪ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያዎች 3,000፣ ለሎት 2፦ የደንብ ልብስ 500፣ ለሎት 3፡- ፕላንት ማሽነሪና መሳሪያዎች 3,000፣ ለሎት 4፡- የህንጻ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች መግዣ 3,000፣ ለሎት 5፡- ፕላንትና ማሽነሪ ጥገና 1,000 በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከ01 /አንድ/ ኮፒ ጋር በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ተወዳዳሪዎች የሚያስገቡትን ደረጃቸውን የጠበቁ እቃዎችን ናሙና በተዘጋጀው ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 558 28 51 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒከ ጀርባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ
ይግባኝ ኮሚሽን
