የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሲኖ ሀይድሮ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ በቀረጥ ነፃ መብት ወደ ሀገር ውስጥ አስጉብተው ከታለመለት አገልግሎት ውጪ ሲጠቀሙበት ተይዘው የተወረሱ 4 EXCA- VATOR ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የአዳማ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 11/2017
የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሲኖ ሀይድሮ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ በቀረጥ ነፃ መብት ወደ ሀገር ውስጥ አስጉብተው ከታለመለት አገልግሎት ውጪ ሲጠቀሙበት ተይዘው የተወረሱ 4 EXCA- VATOR ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
- በአዳማ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ በቀረቡት Excavator ማሽነሪዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡት ማሽነሪዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስከር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆነ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ እያስፈልግም፡፡
- የግልጽ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳቦችና ዋስትናዎች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመግዛት በጨረታው የወጡትን Exca-vator ማሽነሪዎች ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታ ሽያጭ የማሽነሪዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
- በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ Excavator ማሽነሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5) በኢትዮጵያ በተመሰከረለት (CPO Customs Commission Adama branch office ስም በማሰራት ለግልፅ ጨረታ በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ እንድታስገቡ፡፡
- በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት Excavator ማሽኖች የሚገኙበት ቦታ በአዳማ እርዳታ ማስተባበሪያ ጀርባ ቻይና መጋዘን ውስጥ ስለሚገኙ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ሳጥኑ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በ4፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን፤ ነገር ግን ስምንተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቦታ በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው መጋዘን ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቶች ካልቀረቡ ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- በአርጅናል ሰነድ ያልተሞላ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም::
- ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይም የሌላ ተጫራችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች ወይም እኩል የመነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
- አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፣ ለተሸናፊ ተጫራቶች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 12 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ማንኛውም ተጫራች 100 ብር ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ከሌሎች ሰነዶች ጋር አያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት
