የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የተለያዩ የመኪና ጎማዎች በዘርፉ የተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዞኑ ለሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የተለያዩ የመኪና ጎማዎች በዘርፉ የተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዞኑ ለሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በተወዳዳሪዎች ሕግና ደንብ መሠረት የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
2. በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
3. የ2016/17 ዓ.ም ግብር አጠናቅቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታክስ ከፋይነት /TIN/ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
4. ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ የዕቃ ዓይነት 2% በተረጋገጠ /CPO/ ከማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማሰታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አሥራ አምስት የሥራ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡
6. ለአንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከመ/ቤቱ ግዥ ክፍል (G+1/ ምዕ/ወ/ዞን/ገ/ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ምዕ/ወ/ዞገ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስገብተው ለማስገባታቸው መመዝገብ አለባቸው፡፡
8.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት በመግለጽ በተለያዩ ፓስታ ላይ በኦርጅናሉና በኮፒው ላይ በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ተወካይ ፊርማና ማህተም አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሽግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. የሚያቀርቡት ዋጋ ሰነድ ቫትን ያጠቃለለ መሆን አለበት፡፡
11. የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
12. የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የተጫራቾች አለመገኘት በጨረታው መከፈት ላይ የሚያስከትለው ተፅኖ አይኖርም፡፡
13. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፈ ከሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብና የስምምነት ማረጋገጫ ባቀረቡት አጠቃላይ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 057 771 0247 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈል ወይም ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
