በደ/ብ/ብ ክ/መንግስት የሬድዮ ቴለኤቭዥን ድርጅትየዋካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ለቢኢሮ አገልግሎት የሜሉ የተለያዩ ዕቃዎች ፦ የሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ለመወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸው።
2. የቫት ወይም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወም ቲን ተመዝጋቢ የሆኑ።
4. አግባብነት ያለው የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው።
5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የዕቃው ዓይነት ሥም የተመሰረተ ሀገር የሞዴል መለያ የሚያመለክት መግለጫ በግልጽ ማጻፍ ይኖርበታ፣
6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈረም ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች አሻሚና ግልጽ ባልሆኑ ሁኔታው የጨረታ ዕቃ ዋጋ በመሙላት መወዳደሪያ ወይም ለመወዳደር መሞከር ወድያውኑ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
8. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ዕቃ ዋጋ መሙላት የሚችሉት በመ/ቤቱ በተዘጋጀው በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብቻ ነው።
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የዋጋ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል እይችሉም።
10 ተጫራቾች የመጨረሻ ዕቃ ርክክብ የሚፈፀመው ተፈትሾ የቀረበውን ዕቃ ኦርጅናል ወይም አንደኛ ደረጃ መሆኑን ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
11. የጨራታን ሥራን ሆን ብሎ ከጨረታ ማሻጊያ ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የጨረታ ሥነ ሥርዓትን ማወክን መረበሽ ከውድድር ውጪ ያደርጋልበህግም ያስቀጣል።
12. ይህ ጨረታ በማስታወቂያና ጋዜጣ ላይ በወጣ በ111ኛው ቀን 4፡00ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል። ዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት አያስተጓጉልም።
13 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
14. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡበትን ዋግ አ ሁለት መቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ኦርጅናል ዶክመንት ፓስታ ውስጥ በማድረግ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
15. ጨረታው ካሸነፉ በኋላ ዕቃውን ለሚቀርበው ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO አይመለስም።
16. ተጫራቾች ለሚያቀርቡ ዕቃዎች አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ያሸነፉበት ዕቃውች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ገቢ ሳያደርግ ቢወሩ ውል ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ በግዥ ደንብና መመሪያ መሠረት ወደ ተቋሙ ገቢ ተደርገው ለሁለተኛ አሸናፊ ወይም ተጫራች ይሰጣል።
17 . አሸናፊ ተጫራቾች ከአጫራቹ መሥሪያ ቤት ጋር ውል ይገባል መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰውረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
