Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 May 2023, 12:21 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአሰላ ከተማ የሽያጭ ማዕከል እድሳት (Shop rebranding) ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአሰላ ከተማ የሸያጭ ማዕከል እድሳት (Shop rebranding) ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

የጨረታ መለያ ቁጥር RFQ - 4239688

በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ ፣ ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ አንድ አመት የስራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራhተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 02 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

መስፈርት፦

  1. ጨረታው ከሚያዚያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 02 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲፒኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸዉ ላይ ስማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸዉን በትክክል ጽፈዉ መፈረም አለባቸዉ።
  6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለዉ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 02 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-111-09-94 / 022-112-16-60 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

Save Tender