Tender Detail

Tender Details

  • Deadline29 Apr 2023, 11:40 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የግቢውን የግንብ አጥር ማስጠገን ይፈልጋል


ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- መድ/አጠ 2ኛ/ደረ/ት/ቤት 04/2015 ዓ/ም

በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የግቢውን የግንብ አጥር ማስጠገን ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማስያዝ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን በደብዳቤ መሳተፍ የምትፈልጉ ካደራጃችሁ አካል ለትምህርት ቤታችን የተጻፈ ደብዳቤ መቅረብ አለበት።

ስለሆነም ተጫራቾች፦

  1. በግንባታ ስራ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ማለትም /ከ1-7/ መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ መሆን አለበት።
  8. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
  9. ተጫራቾች ከምህንድስና ግምት 20% በላይ ከፍ አድርገው ሞልተው ቢያሸንፉም ዋጋው ተቀባይነት አይኖረውም።
  10. ተጫራቾች ከምህንድስና ግምት 20% በታች አውርደው ሞልተው ካሸንፉም ዋጋው ተቀባይነት ባይኖረውም። ነገር ግን እንደ አስፈላጊነቱ ተቀባይበት ካገኘ የሚያሲዙት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋው 20% ይሆናል።
  11. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 17 የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
  12. ት/ቤቱ ከሚያሰራው ስራ ላይ ከውል በፊት 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  13. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በወሰዱት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ዋጋውን በመሙላት የድርጅቱን ሙሉ ማስረጃ የታሸገው ፖስታ ላይ በመጻፍ ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማስቀመጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  14. አሸናፊው ድርጅት ስራውን በሚሰራበት ጊዜ ነባሩ ግንብ እና ሌሎች ንብረቶች ላይ ምንም አይነት ጉዳት ካደረሰ በራሱ ወጪ መልሶ እንዲያስተካከል ወይም አንዲተካ ይገደዳል።
  15. አሸናፊው ድርጅት የጥገና ስራውን ሰርቶ በሚያስረክብበት ጊዜ የስራው ሁኔታ ት/ት ቤቱ ያስቀመጠውን የስራ ዝርዝር መሰረት ያላደረገ ወይም ጥራቱን ያልጠበቀ አፈጻጸም ሆኖ ከተገኘ ት/ት ቤቱ ስራውን አይረከብም።
  16. አሸናፊው ድርጅት የጥገና ስራውን ሰርቶ አጠናቆ ካስረከበ በኋላ ስራው በቀላሉ ብልሽት ቢያጋጥመው በራሱ ወጪ ስራውን መልሶ እንዲያስተካከል ይገደዳል።
  17.  የትምህርት ቤቱን የጨረታ መመሪያ ከብ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከፖስታው ጋር ማስገባት አለባችሁ።
  18. ጨረታው በ10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  19. ት/ት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ቶታል ፊት ለፊት ይገኛል።

ስልክ፦ 011 259 55 94 / 011 259 34 38

በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት

Save Tender