የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለው በጀት የተለያዩ አይነቶች የጽህፈት መሳሪያዎችና አላቂ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ፌ/ጠ/ፍ/ግ/ጨ/001/2015
የተለያዩ አይነቶች የጽህፈት መሳሪያዎችና አላቂ እቃዎች ግዥ
- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለው በጀት የተለያዩ አይነቶች የጽህፈት መሳሪያዎችና አላቂ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ከላይ የተጠቀሰውን ግዥ ለማቅረብ (ለማቅረብ) ብቃት ያላቸው አቅራቢዎች በታሸገ የጨረታ ሰነድ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን (ዋናው መ/ቤት) እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡ ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸው በግልጽ የጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ግዥዎች ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት።
- የተፈረመ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል መግቢያ ቅፅ።
- የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሠርተፊኬት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- በ2014/205 የታደሰ የንግድ ፍቃድ
- የአገር ውስጥ ገቢ የታክስ ክሊራንስ ይሆናል።
3. ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በቁጥር 7(ሀ) በተገለፀው አድራሻ ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ። አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለከፍያ በነጻ ይሰጣቸዋል።
4. የጨረታው ሰነድ የሚላከው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር (ዋናው መ/ቤት)፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 6166 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ወይም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር (ዋናው መ/ቤት) ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል።
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 «ለ» በተገለጸው አድራሻ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በ8:00 ሰዓት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ማስገባት ይሆናል። ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) /ያይዘው ያቀርባሉ።
6. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ከፍያ ዋስትና ምትከ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም እና የጨረታው አይነት ተጠቅሶ የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም። በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቁጥር 7 ‹‹ሐ›› በተጠቀሰው አድራሻ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በ8:10 ሰዓት ይከፈታል።
7. ሀ/ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ዳይሬhተር ቢሮ (ዋናው መ/ቤት) ቁጥር 9
ለ/ ጨረታው የሚቀርብበት አድራሻ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 9
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 9
8. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር - +251-11 155 3400
ፖስታ ሣጥን ቁፕር 6166 አዲስ አባ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
