የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መድኃኒቶች ፣ የተለያዩ የላብራቶሪ ሬኤጀንት ፣ የተለያዩ የቤት ውስጥ ሴራሚክ ንጣፍ ጥገናና የዲችቦይ ክዳን ስራዎች እና የእሳት አዳጋ መከላከያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ መድኃኒቶች ፣
- የተለያዩ የላብራቶሪ ሬኤጀንት ፣
- የተለያዩ የቤት ውስጥ ሴራሚክ ንጣፍ ጥገናና
- የዲችቦይ ክዳን ስራዎች እና የእሳት አዳጋ መከላከያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዚህ ጨረታ የሚወዳደሩ ድርጅቶች፡-
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቅድ ያላቸውና ለግንባታ ዘርፍ ስራዉ ደረጃ 7 እና በላይ የሙያ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD/ ሰርተፊኬት ያላቸው።
- አጠቃላይ የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር )እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1- 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማንኛውንም ግብር ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡15 ይታሸጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ በዓል /ዝግ /ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ (ማብራሪያ) ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 5738/058 222 0916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል
