የቤት ሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ እቴነሽ አየን እና በፍ/ባእዳ የምስራች አየን መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ የባለ እዳው ንብረት የሆነውን ቤት በቡሬ ከተማ ቀበሌ 04 ክልል ውስጥ የሚገኙውን የፍርድ ባለ እዳ ንብረት የሆነውን አዋሳኙ በምስራቅ ይርጋ በሪሁን በምዕራብ መንገድ በሰሜን አማኑ በደቡብ አያልነሽ የሚያዋስነውን መጠኑ 500 ካሬ ሜትር የሆነውን የግምቱ መነሻ ዋጋ 875,250 (ስምንት መቶ ሰባ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) ሆኖ ነሀሴ 11/2014 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልፅ ጨረታ ይሸጣል።
ስለዚህ የባለእዳውን ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን አሸናፊው እንደታወቀ የሽያጭ ገንዘብ ውስጥ ቢቻል ሙሉውን ካልተቻለ ¼ኛውን በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍርድ ቤት በሞዴል 85 የሚያስይዝ መሆኑን እናሳውቃለን።
ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍርድ ቤት
