Tender Detail

Tender Details

  • Deadline29 Aug 2022, 5:42 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ሄርዳዊት አሰፍሃ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ጀመር ተ/ሚካኤል መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጕዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 89212 በ15/7/2014 ዓ.ምእና በመ/ቁ 82023 በ14/6/2014 ዓ.ም በዋለውችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የሚገኝ የቤ.ቁ 609 በካ/ቁ ETH0000000000-0004081577408151 ልዩ መለያ ቁጥር AA0001040501942 የሆነ መኖሪያ ስፋቱ 346 ካ.ሜትር ይዞታ 84.5 ካ.ሜ ለወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ቦታ የተከለለ ስለሆነ 23.3 ካ.ሜትር ውስጥ ለውስጥ መንገድ የሚቆርጠው በሆኑ 238.2 ካ.ሜ ቀሪ ይሆናል የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,462,000 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልላ ሁለት ሺ ብር ) ሆኖ የትራንዛሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንh በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

Save Tender