የጥቁር ዓባይ ኮንስትራክሽን አ.ማ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና ዕቃዎች ፣ ተሳቢ ፣ ጎማዎች ፣ የተለያዩ መፍቻዎች ፣ የማሽነሪ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና ዕቃዎች ፣ ተሳቢ ፣ ጎማዎች ፣
የተለያዩ መፍቻዎች ፣ ማሽነሪ እና ተሽከርካሪ መለዋወጫ
ዕቃዎችን ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ቁጥር 02/2014
የጥቁር ዓባይ ኮንስትራክሽን አ/ማ /በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ/ በአዲስ አበባ ሳሪስ ማዕከላዊ ጋራዥ ፣ በቃሊቲ ንብረት ማከማቻ መጋዘን፣ በአቃቂ ጠጠር ማምረቻ በበደሌ ቢራ ፋብሪካ ፣ ነቀምት እና ጊቤ ፕሮጀክት ሳይት ውስጥ የሚገኙትን
- የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና ዕቃዎች ፣
- ተሳቢ ፣ ጎማዎች ፣ የተለያዩ መፍቻዎች ፣
- የማሽነሪ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም -
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ሳሪስ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ አጠገብ ከሚገኘው የአ/ማህበሩ ቢሮ ቁጥር 8 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረቶች የጨረታ ሰነድ በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት አዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት ንብረት ክፍል የሚሰጠውን የመግቢያ ወረቀት በመያዝ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ (10%) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ በድርጅቱ ትክክለኛ ስም (BLUE NILE CONSTRUCTION SHARE COMPANY) በማሠራትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በግልጽ በመጻፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ያላስያዙ ተጫራቾችን ኮሚቴው ከጨረታው ይሰርዛል፡፡
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን የገበትን ዋጋ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች በውጤቱ መሠረት ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በሚወጣው የማስረከቢያ ፕሮግራም መሠረት አንስተው ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡ በፕሮግራሙ መሠረት ሳያነሱ ቢቀሩ ለሚፈጠረው ችግር መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ በዚሁ ቀን ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ስለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር፡-011 442 6332
ጥቁር ዓባይ ኮንስትራክሽን አክስዮን ማህበር
