በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ለመግዛት ፍላጎት ያለው ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 5,000(አምስት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ 50 (ሃምሳ) ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 771 0586/082/083
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ /ወራቤ/
