ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በባህር ዳር ከተማ ለሚገኘው የ ’’OncoE6 Cervical Test’’ ማምረቻ ፋብሪካ የ ISO 13485:2016 ዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ ዙር የምስክር ወረቀት (Initial Certification Audit) ለመስጠት የሚያስችል ብቃትና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የብቃት ማረጋገጫ ሰጪ አካላት (Certification Bodies) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኋ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል መንግስት የበጀት ድጋፍ የተቋቋመ እና በክልሉ የልማት ድርጅቶች ማዕቀፍ ስር የሚገኝ ሲሆን በጤና አገልግሎት እና ምርት ላይ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የህክምና መድኃኒቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ሪኤጀንት እና ኬሚካሎችን በሶስት ማሰራጫ ጣቢያዎች ባህርዳር፣ ደሴ እና ጎንደር ክላስተሮች ለሚገኙ ጤና ተቋማት በማቅረብ ይታወቃል፡፡ ይህን ተግባር ለመወጣት በ2019 ዓ.ም ለ አንድ (1) ዓመት ለሚቆይ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አምራች ፋብሪካዎች፣ ኢንተርናሽናል ድርጅቶች ህጋዊ እውቅና ካላቸው አስመጭዎች (Importers) ጋር በጨረታ ህግ መሰረት ውል ይዞ መስራት ይፈልጋል፡፡