የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር (EAA) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ያሉቤቶች ወይም የቢሮ ቦታዎችን አገልግሎታቸው ለስልጠና እና ጥናት እና ምርምር ማዕከል ሊውል የሚችል ለመግዛት በአካባቢው የሚገኙ ህጋዊ የንብረት ባለቤቶች፤ ግለሰቦች ወይም የንብረት ወኪሎች በተዘጋጀው ጥሪ መሰረት ጨረታ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃብሄር ጉዳይ ችሎት በአዳማ ከተማ ደምበላ ከ/ከተማ ኢሬቻ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን ቤት በጨረታ አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን እየገለጽን መግዛት የሚፈልጉ ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ስሙ ላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማእከል ውስጥ ያስገነባቸውን ለባንክ አገልግሎት የሚውል የንግድ ቤት መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል ።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ቁጥር 2 ላፍቶ ሁለገብ ገበያ ማእከል ያስገነባቸውን ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች ንግድ ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን በክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአፈፃፀም ክስ ጉዳይ ምክንያት በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 01 ክልል ውስጥ የሚገኘውን ቤት እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ በሐራጅ መሸጥ አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስማድል ኮሚውኒኬሽን ተርሚናል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለአለበት ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 መገናኛ አካባቢ አምቼ ፊት ለፊት ለዋና አስፓልት መንገድ በጣም ቅርብ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኘውን G+4 መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሚያስተዳድራቸው ነባር ቤቶች መካከል ለመኖሪያ ወይም ለንግድ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ 2 ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ሽ/002/2017 አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በአፈፃፀም ከሳሽ አቶ እስጢፋኖስ ካሎ እና ከአፈፃፀም ተከሳሽ አቶ ዳዊት በለጠ መካከል ባለው የአፈፃፀም ክስ መነሻነት ሆኖ በወላይታ ዞን የሚገኘውን ቤት በጨረታ የሚሸጥ ስለሆነ ቤቱን መግዛት የምትፈልጉ በዚህ ጨረታ ላይ እንድትሳተፉ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጥሪውን ያቀርባል።
የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍታብሔር ጉዳይ ችሎት የአፈጻጸም ከሳሽ ገነት ጀንበሩ እና የአፈጻጸም ተከሳሽ መስከረም በጋሻው መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክርክር በተመለከተ በኮዮ ፈጬ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኝ ኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ስለሚፈልግ ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ ሰዎች በዚህ ጨረታ ላይ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ጉዳይ ችሎት በአፈፃፀም ከሳሽ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ አስቻለው ሸዋ ኔሪ ጣልቃ ገብ ነፃነት ረጋሳ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክርን በተመለከተ የዚህ አፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት የሆነው ባለ ሦስት ወለል (ጂ+3) ህንጻ እና በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ውስጥ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ በጨረታው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
የነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በአፈፃፀም ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ታራኒዮ ወረዳ 3 አለም ባንክ አከባቢ ስልጤ ሰፈር አንሻ መስጊድ አካባቢ በኮብል እሰቶን መቶ ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ መኖሪያ እና የንግድ ቤት የሚሸጥ ስለሆነ ለመግዛት የምትፈልጉ ሰዎች በዚህ ጨረታ ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
በአፈጻጸም ክስ መነሻነት ሆኖ በሶዶ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ህብረት ቀበሌ ጎተራ መንደር በግራ ቀኙ ክርክር ዋስ የሆኑት አቶ ማቴዎስ ኤንኩ እና ወ/ሮ ማስረሻ ማሞ ስም ተመዝግቦ ያለው መኖሪያ ቤት በጨረታ የሚሸጥ ስለሆነ ቤቱን ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ, በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 የሚገኘውን የጋራ መኖሪያ ቤት (ኮንዶሚኒየም) ግልጽ የሆነ ጨረታ ተካሄዶ በመሸጥ በቤቱ ላይ ያለው የባንክ ዕዳ ከተከፈለ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ለግራና ቀኝ ለማካፈል ስለተፈለገ በዚህ ጨረታ ላይ በመሳተፍ መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
በአፈፃፀም ከሳሽ እነ መህድያ አንደታ (7) ሰዎች እና በአፈፃፀም ተከሳሽ ወ/ሮ ከበቡሽ ተሰማ መካከል ባለው የውርስ ንብረት ክስ ክርክር ጉዳይ 250 ካ/ሜ ቦታ ላይ የሚገኘው ቤት የሚሸጥ መሆኑን በማስታወቂያ እንዲወጣ ሲል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍታብሄር ችሎት አዟል፡፡
በአፈጻጸም ክርክርን በተመለከተ በነቀምቴ ከተማ 04 ቀበሌ ውስጥ በፍርድ ባለእዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 376 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ቀርባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን ፍርድ ቤት ያሳውቃል፡፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ለድርጅት 3,527.94 ካ.ሜ እና ለመኖሪያ 210.39 ካ.ሜ ጠቅላላ ስፋታቸው 3,738.33 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያና ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስማቸው ከዚህ በታች የተጠቀሰው ተበዳሪ ያለባቸውን ብድር በወቅቱ ባለመክፈላቸው ምክንያት ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 626/2001 አንቀፅ 28 (1) እና በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው መብት መሰረት ለብድሩ በዋስትና የያዘውን ቤት በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ጫጫን ጨምሮ በሁሉም ክ/ከተሞች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 እንተፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በከፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፈደል ተራ ከ “ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም (ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት/ የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የሸ/ከ/አስተዳደር ከተማና መሰረት ልማት ጽ/ቤት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፤