የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ፣ የትምህርትና የፅዳት ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ ቋሚ ዕቃዎችና የላብራቶሪ ዕቃዎች በ7 ሎት በግዢ ጨረታ ቁጥር 0001/2019 በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- 0001/2019
የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም:-
- ሎት-1 የደንብ ልብሶች
- ሎት-2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት-3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት-4 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት-5 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች
- ሎት-6 ቋሚ እቃዎችን
- ሎት-7 ልዩ ልዩ የላብራቶሪ እቃዎች
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ተጫራቾች:-
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፍበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት።
- ይህ ጨረታ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት /በሂሳብ ቁጥር 1000014692731 ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በማስገባት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 በፋይናንስ በማወራረድ በትምህርት ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2:30-11:30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆነውን በየሎቱ ከታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
1 ሎት 1- የደንብ ልብስ 42,000 2 ሎት -2 አላቂ የቢሮ እቃዎች 20,000 3 ሎት -3 አላቂ የትምህርት እቃዎች 16,000 4 ሎት -4 አላቂ የፅዳት እቃዎች 20,000 5 ሎት -5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 8,000 6 ሎት -6 ቋሚ እቃዎች 20,000 7 ሎት-7 ልዩ ልዩ የላብራቶሪ እቃዎች 6,000 - ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበሪያ CPO እንደሚወረስበት ማወቅ አለባቸው።
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማፃፍ፣ እና ለማያመርቱት ምርት /ዕቃ/እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መሳተፍ ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ በ11ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 በትምህርት ቤቱ በፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 22 ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-4-71-61-31/011-4-34-30-96 አድራሻ፡ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከወረዳ ሁለት ፊት ለፊት በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
አቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Akaki Biruh Tesfa Primary School, Akaki Kality, Addis Ababa, buys in seven lots by open tender: uniforms, office and school consumables, cleaning items, various tools, fixed items and lab items. Bidders need supplier registration, a renewed sector licence, paid tax and VAT.
