የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጽህፈት መሣሪያ፣ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የህትመት ሥራዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ደንብ ልብስ፣ የፎቶ ኮፒ አገልግሎት/አውት ሶርስ/ና የመኪና ዘይቶች በ9 ሎት በጨረታ ቁጥር ደወ/ከፍ/425/2019 በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር :ደወ/ከፍ/425 /2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የተዘረዘሩትን እቃዎችና እንዲሁም የፎቶ ኮፒ አገልግሎት የፍትሐብሄር፣ ወንጀል፣ኮፒ አየተደረጉ ለሚመለከተው አካል የሚተላለፍ መዝገቦችን ኮፒ ማድረግና ለዚህ አገልግሎት የቤት ኪራይ የመብራት ወጪዎችን በመ/ቤቱ ይሸፍናል። በዚህ መሰረት መ/ቤቱ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ሎቶች ለማጫረት ይፈልጋል:- ማለትም ሎት1 የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ ሎት 2 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎችን፣ ሎት 4 የህትመት ስራዎችን፣ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ ሎት 6 የመኪና እቃ መለዋወጫ፣ ሎት 7 የደንብ ልብስና ተዛማጅ እቃዎችን፣ሎት 8 የፎቶ ኮፒ አገልግሎት/አውት ሶርስ/፣ ሎት 9 የመኪና ዘይቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን መ/ቤቱ ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ፤
- የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው መጠን ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል ፤
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ደ/ወ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ግዥና ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 121 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 ጽህፈት መሳሪያዎችን 12000/አስራ ሁለት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 2 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን 4000 /አራት ሺህ ብር ብቻ/፤ ሎት 3 የጽዳት እቃዎችን 3600/ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ብር ብቻ/፤ ሎት 4 የህትመት ስራዎች 7000/ሰባት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት5. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 10000/አስር ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 6 የመኪና እቃ መለዋወጫ 30000/ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 7 የደንብ ልብስና ተዛማጅ እቃዎች/ 6000/ ስድስት ሺህ ብር ብቻ ፣ሎት 8 የፎቶ ኮፒ አገልግሎት/አውት ሶርስ/ 8000 /ስምንት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 9 የመኪና ዘይቶች 4000 /አራት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከ73 ቀን ያላነሰ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት "ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም ። ሆኖም በሎቱ ውስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ውስጥ አንድ ዕቃ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ ድርጅት ከጨረታ ውጪ የሚሆን ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን / ሰነዱን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ወ/ዞ/ከ/ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 412 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ላይ በይፋ ይከፈታል፤ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ በይፋ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ነው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ድምር ካላስቀመጡ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ላይ የአንድ ዋጋም ጠቅላላ ዋጋም ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጪ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ መመሪያ የተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና የግምገማ ዘዴና መስፈርት በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 033-111-44-28 ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-82-21 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
✨ messages.ai_summary
South Wollo Zone High Court, Amhara, buys in nine lots by open tender: stationery, fixed and consumable items, cleaning items, printing, electronics, vehicle parts, uniforms, an outsourced photocopy service and vehicle oils. Bidders need a renewed licence, TIN, tax clearance and VAT.
