እናት ባንክ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ B+G+2 መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ (ለሁለተኛ ጊዜ)
Enat Bank S.C (እናት ባንክ አ.ማ)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የእናት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 ለባንኮች በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
| የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ለጨረታ የቀረበው ንብረት | ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ቀን ዓ.ም | ሰዓት |
| [...] ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማኅበር | አቶ ብርሃኑ ሳሙኤል | [...] ቅርንጫፍ | B+G+2 መኖሪያ ቤት | አ/አ | ቦሌ | 07 | [...]/7/29/3/7/1/18 42/2545/ 28316 /03 157 | 157 ካ.ሜ | 28,000,000 | ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም | ከ[...] 4:00-5:15 |
የሐራጅ ደንቦች
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ ሰዓት አስራ አምስት ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ አስራ አምስት ደቂቃዎች የተጫራቾች ምዝገባ አይካሄድም።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት:: ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል::
- ሐራጁ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ንብረቱ ባለበት ቦታ ይካሄዳል::
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው::
- በንብረቱ ሽያጭ ላይ ለመንግስት የሚከፈለው የሊዝ ክፍያ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ክፍያዎችን የስም ማዛወሪያን ጨምሮ ገዢው /አሸናፊው /ይከፍላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከህግ ክፍሉ ጋር እና/ወይም ከቅርንጫፎቹ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-558-65-68 / 0115523472 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
የእናት ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Enat Bank is auctioning, for the second time, a foreclosed B+G+2 residential house on a 157 square metre plot in Bole sub-city, Woreda 07, Addis Ababa. Bidders deposit a quarter of the starting price by CPO. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
