በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-አዲስ አበባ ነጭ የዳቦ ስንዴ የምግብ እህል የሃገር ውስጥ ምርት ከአቅራቢዎች ከነመቋጠሪያው በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Agricultural Business Corporation Seed Supply Sector
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
ስንዴ የምግብ እህል ግዥ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-የም/ዘ/አ/ዘ/ምዘ/ሽ01/2019
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-አዲስ አበባ ነጭ የዳቦ ስንዴ የምግብ እህል የሃገር ውስጥ ምርት ከአቅራቢዎች ከነመቋጠሪያው በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ነጭ የዳቦ ስንዴ የምግብ እህል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት(ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል እና በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በመንግስት ግዥ አቅርቦት የተመዘገበ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽ የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዶሮ ተረፈ ምርት(የዶሮ ኩስ) ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00፣ከሰዓት በኋላ ከ7:00-10:30 እንዲሁም ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00- 5:30፣ከሰዓት በኋላ ከ7:30-10:30 በግብርና ግብዓት ግቢ 2ኛ ፎቅ በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በኤንቬሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፣ ጨረታው ህዳር 15/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ጽ/ቤት ጨረታው ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር:- 09-41-00-68-72/09-81-73-70-12
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Agricultural Works Corporation, Seed Supply Sector, buys locally produced white bread wheat (food grain), with bags, from suppliers through a tender in Addis Ababa. Bidders need a renewed sector trade licence, TIN, VAT, tax clearance and supplier registration.
