የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህር ዳር በከተማ አስተዳደ ገንዘብ መምሪያ በከተማ አስተዳደር ስር ላሉ የመንግስት ቤቶች ለሚማሩ ቅድመ አንደኛና በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ምገባ ለማካሄድ ዳቦ እና ወተት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Amhara National Regional State Bahir Dar City Administration Finance Department
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህር ዳር በከተማ አስተዳደ ገንዘብ መምሪያ በከተማ አስተዳደር ስር ላሉ የመንግስት ቤቶች ለሚማሩ ቅድመ አንደኛና በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ምገባ ለማካሄድ ዳቦ እና ወተት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉና መወዳደር የሚችሉ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል:-
- ተወዳዳሪው የተሰማራበትን የንግድ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የዘመኑ የታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- ተወዳዳሪዎች ከተራ ቁጥር 1 - 3 የተጠቀሱትን አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- የሚቀርበው ዳቦ እና ወተት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 46 ማግኘት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና 100,000.00 መቶ ሺህ ብር ማስያዝ አለባቸው፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒክና የፋይናንስ በማለት በሁለት በታሸጉ ኤንቨሎፖች በመለየት፣ ሁለቱንም በአንድ አጠቃላይ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለመለየት እንዲቻል በግልፅ ፅሁፍ አድራሻን በመጥቀስ ዘወትር በስራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 46 በ11ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ይከፈታል
- በዋጋ መሙያ የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስል/ቁ/058-220-93-73 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Bahir Dar City Administration Finance Department buys bread and milk by open tender for school feeding of pre-primary, primary and middle school students in government schools under the city. Bidders need a renewed trade licence, tax clearance, VAT and TIN.
