ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የውሃ ስርገት መከላከያ፣ የውሃ ታንከር ፣ የተለያዩ ፓምፖች እንዲሁም ሌሎች የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦትና ገጠማ ጨረታ ቁጥር 18/2019 ግዥ ለመፈጸም ሕጋዊ ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 18/2019
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የውሃ ስርገት መከላከያ፣ የውሃ ታንከር ፣ የተለያዩ ፓምፖች እንዲሁም ሌሎች የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦትና ገጠማ ጨረታ ቁጥር 18/2019 ግዥ ለመፈጸም ሕጋዊ ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሠዓት ድረስ ብቻ በባ/ዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክ/ከ ዋናው አስፓልት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ዋናው ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዕለቱ 8:00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8:30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8:00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዕለቱ 8:00 ላይ ሳጥኑ ታሽጎ 8:30 የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ዉድድሩ በሎት/በምድብ/ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት/ምድብ/ ለተጠየቁ የሥራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት። ነገር ግን ለኮርፖሬሽኑ ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ከታመነበት በግዥ መመሪያው መሠረት ውድድሩን በነጠላ ዋጋ በማወዳደር ዝቅተኛ የሆነውን በመምረጥ ግዥ ሊፈፀም ይችላል።
- የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር ባህር ዳር- 058-218-0538 /09-21-25-89-20
አዲስ አበባ ማስተባበሪያ :- ስልክ ቁጥር 01112655338
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Zemen Construction Corporation (Bahir Dar) seeks manufacturers and suppliers to supply and install waterproofing materials, water tankers, various pumps and other sanitary items for its projects, by open tender. Bidders need a renewed sector trade licence, TIN and VAT.
