በአፈፃፀም ፍርድ ከሳሽ ወ/ሮ ፍሬህይወት ስለሺ እና 4 ሰዎች እና ተከሳሽ ወ/ሮ የወርቅውሃ ወሌ መካከል ባለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ፣ በሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክፍለ ከተማ፣ ኤጀርሳ ጎሮ ወረዳ የሚገኝ የካርታ ቁጥር A-95-4114/84፣ የቤት ቁጥር 7415፣ 865.5 ካሬ ሜትር መኖሪያ ቤት በጨረታ ይሸጣል።
በሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ጉዳይ ቡድን
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ፍርድ ከሳሽ ወ/ሮ ፍሬህይወት ስለሺ እና 4 ሰዎች እና በፍርድ አፈፃፀም ተከሳሽ ወ/ሮ የወርቅውሃ ወሌ መካከል ያለውን የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ አስመልክቶ በሸገር ከተማ አስተዳደር፣ በቡራዩ ክፍለ ከተማ በኤጀርሳ ጎሮ ወረዳ አስተዳደር የሚገኝ፣ የካርታ ቁጥሩ A-95-4114/84፣ የቤት ቁጥር 7415 የሆነ ስፋቱ 865.5 (ስምንት መቶ ስልሳ አምስት ነጥብ አምስት) ካሬ ሜትር የሆነ፣ ወሰኑ በምዕራብ ወ/ሮ ፎዝያ ከማል በደቡብ በግል ንብረት የሚዋሰን በሰሜን በመንገድ የሚዋሰን መኖሪያ ቤትን የበረክ ወረዳ አስተዳደር በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም መነሻ የጨረታ ዋጋ 15,000,000 (አስራ አምስት ሚሊዮን) ብር በማድረግ በ18/02/2019 ዓ.ም የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት በጨረታ ለመሸጥ ስለፈለገ በዚሁ መሠረት ጨረታውን ለአንድ ወር ክፍት አርጎ በማቆየት በ07/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት አንስቶ እስከ 6:30 ሰዓት ድረስ መጫረት ለሚፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው የመኖሪያ ቤት አድራሻ በመገኘት በፍትሐ ብሔር ስነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 440/1 መሠረት የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመሸጥ ስለፈለገ ለመግዛት የሚመጡ ሰዎች በጨረታ ዋጋ ከተሸጠበት ውስጥ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) ወዲያውኑ በባንክ CPO (በክፍያ ማዘዣ) መክፈል እንዳለባቸው እና ለጨረታው አሸናፊ ወዲያውኑ የሚከፈል የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት አዟል።
