የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የካ ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ቁጥር/ቅ/ጽ/አ/አ/ት/ቢ/የካ/ቅ/ጽ/ቤት/ግጨ/01/2019 በሎት 1 (አንድ) ደንብ ልብስ፣ በሎት 2 (ሁለት) የጽህፈት መሳሪያ/ የፕሪንተር ቀለሞች እና ሎት 3 (ሶስት) የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/አ/ት/ቢ/የካ/ቅ/ጽ/ቤት/ግ/ጨ/ቁ/01/2019
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የካ ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ቁጥር/ቅ/ጽ/አ/አ/ት/ቢ/የካ/ቅ/ጽ/ቤት/ግጨ/01/2019 በሎት 1 (አንድ) ደንብ ልብስ፣ በሎት 2 (ሁለት) የጽህፈት መሳሪያ/ የፕሪንተር ቀለሞች እና ሎት 3 (ሶስት) የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ ሲሆን:-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባችሁ።
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4:00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን::
- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የካ ቅ/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 602 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10:00 ሰዓት በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (አንድ) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 (ሁለት) ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) እና ለሎት 3 (ሶስት) ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መፈረም አለባቸው።
ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- 22 ማዞሪያ መከሊት ህንጻ ጎን ፕሪሚየም ኮሌጅ ያለበት ህንጻ ላይ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 602
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-10-50-28-12 መጠየቅ ይቻላል::
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የካ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Transport Bureau, Yeka branch office, buys in three lots through an open tender: uniforms (Lot 1), stationery and printer toner (Lot 2) and cleaning supplies (Lot 3). Bidders need a renewed trade licence, TIN, supplier certificate, tax clearance and VAT certificate.
