የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለተሽከርካሪና ማሽነሪ አገልግሎት የሚውል ጎማ ግዥ
Menkorer Construction Enterprize (የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግሥታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለድርጅቱ ለተሽከርካሪ እና ማሽነሪ አገልግሎት የሚውል ጎማ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት:-
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 እና አዲስ አበባ 4ኪሎ አልማ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤ ሆኖም የጨረታ ፖስታው ገቢ የሚሆነው እና ጨረታው የሚከፈተው ደ/ማርቆስ ከተማ ድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ነው::
- ተጫራቶች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ማስገባት አለባችሁ::
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ታሽጎ 3:30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ በበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል:: ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመከፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም::
- ተጫራቶች በዘርፉ ሕጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የኒጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቶች ያሸነፉትን ጎማ ድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ አለበት::
- ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋዉን 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው::
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው ጎማ በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት::
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል::
- ተጫራቶች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው::
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ለደ/ማርቆስ በስልክ ቁጥር 0920514407/0953601984 ለአዲስ አበባ በስልክ ቁጥር 0955274444 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤ በደ/ማርቆስ ከተማ/አስተዳደር መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Menkorer Construction Enterprise, a state development enterprise in Debre Markos (Amhara), seeks suppliers of tyres for its vehicles and machinery, by lot or in bulk. Bidders need a renewed trade licence, TIN and VAT registration and must deliver to the head office. National open bid.
