በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ የሆነው በጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህንጻ ለማስጠገን በዘርፉ በደረጃ GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፤
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ የሆነው በጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህንጻ ለማስጠገን በዘርፉ በደረጃ GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፤
ስለዚህ በመስኩ የተሠማራችሁ ተጫራቾች፣
- ደረጃቸው GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈለና የ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- በከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር የተመዘገቡና የ2019 ዓ.ም የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የ2018 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፤
- በክልሉ እና በዞናችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ መሆን ይገባቸዋል፤
- የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዘውትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ22ኛው ቀን ይሆናል::
- ኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት፤
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ለ21 ተከታታይ ቀን ከዋለበት በኃላ በ22ኛ ቀን ከረፋዱ 4:00 ታሽጎ 4:30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ለ90 (90+28) ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ፤በኢንሹራንስና በቼክ ዋስትና መቅረብ አይቻልም፤
- ጨረታዉ የሚገመገመዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማብራሪያና ማሻሻያ በተደረገው መሠረት ነዉ::
- በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ይደርጋል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0461310108 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
✨ messages.ai_summary
Gedeo Zone Finance and Plan Department seeks GC/BC grade 5 and above contractors for building works on the Gedeo Zone Police Department building. Bidders need renewed trade licence, TIN, VAT, Ministry of Urban and Infrastructure licence, supplier registration and tax clearance.
