የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል::
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ተቋ 001/2019 ዓ.ም
የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል:: በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ እና የሰው ሀይል የሚያሟሉ በጥቃቅን አነስተኛ ማህበራት ዘርፍ መካከለኛ የእድገት ደረጃ ፣ በጥቃቅን አነስተኛ መብቃት የተደራጁ እና BC-5/GC-5 እና ከዚያ በላይ ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል::
ተቋራጮቹ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
| ሎት | የስራዉ አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና | ደረጃ | የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን | የጨረታ ማስገቢያ ቀን | የጨረታ መክፈቻ ቀን |
| ሎት 1 | ወ/ሮ ቀለመ ወርቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአጥር እና ድጋፍ ግንብ ግንባታ ስራ | 150,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 2 | ወረዳ 02 እና ወረዳ 06 የድጋፍ ግንብ ፣ የመጫወቻ ቦታ ግንባታ ፣ ላይብረሪ ግንባታ | 150,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 3 | የወረዳ 5 ወጣት ማዕከል ህንጻ እድሳት ፣ አጥር ግንባታ፣ የጥበቃ ቤት ግንባታ፣ ስቶር እና ሱቅ ስራ | 100,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 4 | ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ህንጻ እድሳት ስራ | 100,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 5 | የወረዳ 6 ወጣት ማዕከል ህንጻ እድሳት ስራ እና የጥበቃ ቤት ግንባታ | 100,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 6 | ወረዳ 06 አዳራሽ ጥገና | ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ | በጥቃቅን አነስተኛ መብቃት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 7 | የወረዳ 04 የጥበብ እድገት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የስፖርት ሜዳ ግንባታ | 100,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 8 | አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አጥር ግንባታ | 100,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 9 | ወረዳ 2 ጂ+4 ራስ አምባ ጤና ጣቢያ እድሳት | 100,000 ሺህ ብር | በጥቃቅን አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 10 | ወረዳ 2 ጂ+4 ራስ አምባ ሰርቶ ማሳያ ህንፃ ግንባታ | 500,000 ሺህ ብር | BC-5/GC-5 እና ከዚያ በላይ | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
| ሎት 11 | ወረዳ 4 ጂ+4 ፖሊስ ካንፕ ግንባታ | 500,000 ሺህ ብር | BC-5/GC-5 እና ከዚያ በላይ | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት | በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ | በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4:15 ሰዓት ጀምሮ |
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶኩመንቶች ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- በዘርፉ የ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የእድገት ደረጃ ማሳወቂያ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 02:30 ሰአት እስከ 10:00 ሰአት ድረስ ከተራ ቁ.1-4 ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናዉን (orginal) እና የማይመለስ ቅጂ(copy) ይዞ በመቅረብ ከሎት 1-9 በነጻ እና ከሎት 10-11 የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ከአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቀርበው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::
- ጨረታው የሚከፈተው በ22 ኛው የሥራ ቀን በአሰቱ ኮሚቴዎችና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ከረፋዱ 04:00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ 04:15 ሰአት የሚከፈት ይሆናል::
- ማንኛውም ተጫራቾች ለ60 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / BID BOND / በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (UnConditional Bank Guarantee) ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን ማቅረብ ግዴታ አለበት:: የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ዉጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በግንባታና በዲዛይን በንዑስ ተቋራጭነት ለማሳተፍ የወጣውን መመሪያ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ይኖርባቸዋል:: ስለዚህም የሚያሳትፉትን የስራ ዝርዝር በመጥቀስ ከስምምነት ደብዳቤ ጋር አያይዞ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- አስሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ(Instruction to Bidder(ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይገደዳሉ::
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፤ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል:: እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያስርዛል:: በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል::
- ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ረፋዱ 04:00 ሰአት ማስገባት ይኖርባቸዋል:: የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል::
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአራዳ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ባለሙያዎች በድርጅታቸው ውስጥ ብቻ የሚሰሩ ወይም ለድርጅቱ ብቻ የፈረሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በድርጅቱ ሀላፊ ወይም ተመሳሳይ ተግባር እና ስልጣን በተሰጠው አካል እና በተቀባይ ባለሙያ የተፈረመ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: አንድ ባለሙያ ከአንድ ስራ ተቋራጭ በላይ ፈርሞ ከተገኘ ያስፈረሙት ስራ ተቋራጮች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል::
- አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶች አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት ሙሉ መብት አለው::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አራት ኪሎ በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ::
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Arada Sub-city Design and Construction Works Office seeks contractors for 11 lots of building, renovation, fence, retaining wall and sports field works in Addis Ababa. Lots 1-9 for micro and small enterprises; lots 10-11 for BC-5/GC-5 and above; renewed licence, VAT, TIN and tax clearance required.
