Tender Detail

Tender Details

  • Company ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline15 Nov 2026, 4:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ/ማ በተከፈለ ብር 10,228,000 እና በተፈረመ 39,312,000 ብር ካፒታል የተቋቋመና ከ ጃንዋሪ 2025 እአአ ጀምሮ በሥራ ላይ ሲሆን ተቋሙ ለሚቀጥሉት ተከታታይ ሶስት የሂሳብ በጀት ዓመታት (ጁን 2027/2028/2029 እአአ) የፋይናንስ ሪፖርቶችን በውጪ ፐብሊክ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል::

ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ


የውጭ ኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ/ማ በተከፈለ ብር 10,228,000 እና በተፈረመ 39,312,000 ብር ካፒታል የተቋቋመና ከ ጃንዋሪ 2025 እአአ ጀምሮ በሥራ ላይ ሲሆን ተቋሙ ለሚቀጥሉት ተከታታይ ሶስት የሂሳብ በጀት ዓመታት (ጁን 2027/2028/2029 እአአ) የፋይናንስ ሪፖርቶችን በውጪ ፐብሊክ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል::

በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም የውጭ ኦዲተር ምደባ መመሪያ ቁጥር (Appointment of External Auditor of a Microfinance Institution Directive No.) MFI/37/2024 ስር የተጠቀሱትን እና የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ መመሪያ ቁጥር 1096/2017 መሰረት አስፈላጊ መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ የሚያሟሉ ሆነው፣

  1. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ አሰራር መሰረት የፐብሊክ ኦዲተርነት ፈቃድ ያለው
  2. የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የወቅቱ ክሊራንስ፣የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣
  3. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ፈቃድ የተሰጠውና የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣
  4. ድርጅቱም ሆነ የኦዲት ቡድን አባላት የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  5. አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ማቅረብ የሚችል
  6. ሌሎች ከላይ በተጠቀሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ የተጠቀሱ አስፈላጊ መስፈርት፣

ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ 22 ትራፊክ ጽ/ቤት ጀርባ በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራሪያውንና ዋጋ (Technical and financial proposal) ከ አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለበት::

ማሳሰቢያ

  • ተጫራቾች ከመሳተፋቸው በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም የውጭ ኦዲተር ምደባ መመሪያ ቁጥር (Appointment of External Auditor of a Microfinance Institution Directive No.) MFI/37/2024 በዝርዝር መመልከትና ማሟላት አለባቸው::
  • ተቋሙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለወገን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ

+251- 0116674208/+251993518853

✨ messages.ai_summary
External audit of Lewegen Microfinance Institution's financial reports for three consecutive fiscal years. Open to public audit firms licensed by the Accounting and Auditing Board of Ethiopia with microfinance audit experience, renewed trade licence, tax clearance, VAT and TIN.
Not stated in the notice: opening date, bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender