የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የመሰረተ ልማት ማሽነሪዎች እና ትናንሽ መኪናዎች ኪራይ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መሰረተ ልማት የሚሰሩ
- ማሽነሪዎች እና ትናንሽ መኪናዎችን ለመከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ/ መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ም[ስክር] ወረቀት ያላቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት [አስራ] አምስት (15)ተከታታይ የስራ ቀናት ስለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ [ሺህ] አምስ መቶ) ብር በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከኮዬ ፈጬ ክ[ፍለ] ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (በፖስታ) በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት [አስራ] አምስት (15) ተከታተይ ቀናቶች ድረስ በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀ[ው] የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ(ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀን 4፡[30 ሰዓት] ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/[ቤት] ውስጥ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ነገር [ግን] ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈ[ረም] ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ው[ል] ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛው[ም] ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
- የመወዳደሪያ ሰነዱ በጨረታ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መ[ብቱ] የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0114-39-94-93 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Koye Feche Sub-City Finance Office (Sheger City, Oromia) seeks to rent construction machinery and small vehicles for its infrastructure works. Open to firms with a renewed licence, VAT registration and supplier-list registration.
