የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት የውሀ ቦቴ እና አይሱዙ ተሽከርካሪ ኪራይ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጉብሬ ዲስትሪክት 001/2019
በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች እና ጥገና መስመሮች አገልግሎት የሚውሉ የውሀ ቦቴ ፣ ለሰርቪስና ነዳጅ ማመላለሻ የሚሆን አይሱዙ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጋቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና « ኦሪጅናል » እና አንድ ፎቶ ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
- አቀራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ ለለባቸው፣ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፣ የጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 0113220325/0113220327 /0113220328
በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Roads Authority, Gubre District Office, seeks to rent a water bowser and an Isuzu truck for staff service and fuel transport for its road projects and maintenance sections. Open to VAT-registered firms with a relevant trade licence on the supplier list.
