የደንብ ልብስ፣ የቢሮና የፅዳት እቃዎች፣ ህትመት፣ መድኃኒትና ሪጀንቶች፣ የማሽነሪ ጥገና፣ ግንባታና ፓርቲሽን፣ ትራንስፖርት እና መስተንግዶ ግዥ (12 ዘርፍ) - የቂርቆስ ክ/ከተማ ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለ2019ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ
1. ደንብ ልብስ (6211) 2.አላቂ የቢሮ እቃዎች (6212) 3.ህትመት (6213) 4.አላቂ የፅዳት ዕቃዎች (6218) 5.ልዩ ልዩ መሳሪያዎች (6219) 6.ለማሽነሪ እና ለፕላንት ጥገና (6243) 7.ለፕላንት እና ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ (ቋሚ እቃዎች) (6313) 8.አላቂ የህክምና እቃዎች (መድኃኒትና ሪጀንቶች) (6214) 9.ለህንፃ እና ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ጥገና (የግንባታ እና ፓርቲሽን ስራዎች) (6244) 10.ለሙያት አገልግሎት ትራንስፖርት (6255) 11.ለመስተንግዶ (ለጤና ተቋሙ ካፍቴሪያ) (6233) 12.የሮቶ አጥበት እና ጥገና (6245) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰቦች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑ ግብር የገበረ ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና በአቅራቢነት የተመዘገ በማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት ጠቅላላ ዋጋ እና የአንዱን ዋጋ ከፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በሰጠው ፎርም ላይ መሙላት ይኖርበታል። የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች ጨረታውን በትክክል በታሸገ እና ሙሉ አድራሻው በትክክል በታወቀ ኤንቨሎፕ በሁለት ፖስታ በማድረግ ከላያቸው ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው መፃፍ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ያቀረቡት CPO ኮፒ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ወይም ዋስትና ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የእቃዎቹን መስፈርቶች አይነት ሳይለወጡና ሳይነካኩ በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት (ፎርም) ላይ በትክክል ሞልተው ማቅረብ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ለማይቀርብባቸው እቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
- ለጨረታው የቀረበው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በአጋጣሚ ቢሰተካከል በቦታው ፊርማ ሊኖረው ይገባል።
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍፁም አይቻልም።
- ተጫራቾች ጨረታውን በትክክል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ከታች በተ.ቁ 1፣2፣3፣4፣5፣6፣10፣11 እና 12 ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ለተ.ቁ 7 እና 8 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ለተ.ቁ 9 CPO ማቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11፡30 ሰዓት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይሰረዝም።
- መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት እንደታወቀ የጨረታውን ውጤት ወዲያውኑ ያሳውቃል።
- ማሳሰቢያ፡- ኦርጅናል ፖስታዎች በጨረታ መክፈቻ እና መወዳደሪያ ወቅት የማይከፈት መሆኑን እንገልፃለን። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የሚገኝበት ቦታ ቡልጋሪያ አለፍ ብሎ ከፍኘ ማደያ በስተግራ ታጥፎ በሚወስደው መንገድ 150 ሜትር ገባ ብሎ ከሰኒ ሳይድ ት/ቤት ጀርባ ወይም ከኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪ ዝቅ ብሎ ይገኛል።
- ስልክ ቁጥር 011 4 62 49 47
