በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወ/ዞን የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1.በተደጋጋሚ የሚቀየሩ የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ሎት 2.የቀላል መኪና ተሽከርካሪ ጎማ በመደበኛ በጀት በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በራስ ሀይል የግዥ ስልት አወዳድሮ በሎት ድምር ለመግዛት ይፈልጋል::
የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወ/ዞን የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1.በተደጋጋሚ የሚቀየሩ የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ሎት 2.የቀላል መኪና ተሽከርካሪ ጎማ በመደበኛ በጀት በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በራስ ሀይል የግዥ ስልት አወዳድሮ በሎት ድምር ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- ጨረታውን ይፋ ያደረገው የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ነው የተሟላ አድራሻውም በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ከተማ ከደሴ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ቦታ
- የሚወዳደሩበትን እቃዎች በተመለከተ በየሎቱ ሲሆን ርክክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአራቱም ንብረት ክፍል ይሆናል::
- የግዥ ዘዴው ግልጽ ጨረታ ሲሆን የጨረታ መለያ ቁጥሩ መደበኛ 001/2019 ነው::
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ እጩ ተወዳዳሪዎች ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ፣ በዘርፉ የተገለጸ የንግድ ስራ ፍቃድ እና ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ፣ የግዥው መጠን ከብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ብር 300/ሶስት መቶ/ ወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመክፈል መውሰድ ይቻላል::
- የመጫረቻ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ21/02/2019 ጀምሮ እስከ 1/03/2019 4:00 ሰዓት ድረስ ከወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላል::
- የመጫረቻ ሰነዱ የመጨረሻ ማስረከቢያ ቀን 1/03/2019 እና የሚከፈትበት ቀን- 1/03/2019 ሰአት 4:30 ይሆናል::
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታው አከፋፈት ላይ መገኘት የሚችሉ መሆኑን፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ና በተጫራች መመሪያ ላይ በተገለጹት መሰረት ብር 71,385/ሰባ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር/ ለመኪና እቃ ፋስት ሙቪንግ እና ብር 30,030 /ሰላሳ ሺህ ሰላሳ ብር/ ለመኪና ጎማ ማስያዝ አለባቸው::
- ለእቃ ከ20,000 በላይ ግዥ ሲፈጸም 3 ፐርሰንት ለአቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑ
- የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት ያለው ሲሆን በዚህም ምክንያት ተጫራቹ ላወጣው ወጭ መስሪያ ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን
- ተጫራቾችበጨረታው ለመሳተፍ ከተራቁጥር1-11የተጠቀሱትንመረጃዎችንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: የሚቀርበው ፎቶ ኮፒ የሚነበብ መሆን አለበት
- የሚገዙት የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ(ስፔሲፊኬሽን) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ::
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር:- 0332210025 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል::
የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን
✨ messages.ai_summary
Werbabo Woreda Finance Office seeks suppliers for Lot 1 frequently replaced light vehicle spare parts and Lot 2 light vehicle tires, bought by lot via open bid. Bidders need a TIN, relevant business license and registration certificate, and VAT registration if purchase exceeds 500,000 birr.
