የአረቅጥ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሙያ ሥልጠናዎች የሚያገለግሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ
የአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮሌጅ
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተለያዩ ፕሮግራሞችና ሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች ማለትም የሜካኒክስ፣ የአውቶሞቲቭ፣ የአይሲቲ፣ የቢኢአይ፤የኮንስትራክሽን፣ የሰርቬይ የስቴሽነሪ የደንብልብሶች፣ የፅዳትዕቃዎች፣ የመ ኪና መለዋወጫ፣ለሆቴልና ቱሪዝም፣እና ጋርመንት ስልጠና መስጫ እቃዎች፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ ንግድ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል :: በዚሁ መሰረት በጨረታው ተወዳድሮ ለማቅረብ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ና የዘመኑ ግብር መክፈላቸው የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አቅርቦት ጋር ተዛማጅነት ያለው ንግድ ፈቃድ በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን _ ሰርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ስም ሂሳብ ቁጥር 1000133257498 ወይም በአካል ኮሌጁ ድረስ በመቅረብ ገቢ በማድረግ ይህን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ የግ/ን/አስ/ደጋፊ ስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማንኛውም ህጋዊባንክ የተረጋገጠ ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ CPO/ በአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮሌጅ ስም አስሮ ማቅረብ ይኖርበታል::
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ውል መፈፀምና የውሉ ማስከበሪያ አሸናፊ ከሆነባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ከኮሌጁ በሚገዙት የጨረታ ዶክመንት ላይ በመሙላት ዋናው/ኦርጅናል/ እና ኮፒው ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ አድርገው በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በፖስታው ላይ የኮሌጁ ስምና ጨረታ ቁጥር በመፃፍ የንግድ ድርጅቱ ስምና ማህተም በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 20ኛው ቀን ከቀኑ 8.00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ተወዳዳሪ ለውድድር ዋጋ ሞልተው የሚያቀርበው ኮሌጁ በአዘጋጀው የጨረታ ዶክሜንት ላይ ብቻ ሲሆን በእያንዳንዱ የጨረታ ዶክሜንት ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ መደረግ አለበት
- ተጫራቾች ከጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ በማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ ጨምሮ ማንኛውም መረጃ ለውድድር ከሚቀርቡ ኦርጅናል የጨረታ ዶክመንቶች ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 20 ቀን በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዢ ኬዝቲም ክፍል ይከፈታል:: ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል ::
- አሸናፊው ውል ተፈራርሞ ከአጠናቀቀበት ጊዜ አንስቶ በ18 ቀናት ውስጥ የአሸነፈባቸው እቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ኮሌጁ ድረስ አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል::
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ሁኔታ VAT የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርበታል :: በትክክል ካልተገለፀ የተፃፈው ዋጋ ቫትን ያካተተ ነው ተደርጎ ይወሰዳል ::
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ:- 0911068530/0913700666
የአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Areka Polytechnic College seeks suppliers for permanent and consumable training materials across mechanics, automotive, ICT, BEAE, construction, survey, stationery, uniforms, cleaning supplies, machinery spare parts, hotel and tourism, and garment training. Bidders must hold a valid trade license, VAT registration, tax clearance, and supplier registration certificate.
