የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 1147/11፣ 216/92 እና 97/90 መሠረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ በጥሬ ገንዘብ /በካሽ/ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 1147/11፣ 216/92 እና 97/90 መሠረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ በጥሬ ገንዘብ /በካሽ/ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| የተበዳሪው/መያዣ ሰጪው ስም | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የንብረቱ ዝርዝር /መግለጫ/ | የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር) | የሐራጁ ደረጃ | የሐራጁ ቀንና ሰዓት |
| ዲዲጋ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር | ነቀምቴ ከተማ | ድርብ ተግባር ተሽከርካሪ (Toyota Double Cab Vehicle) Model: KUN25L-PRMDHV Chassis: MROFR22G5F0731894 |
3,375,656.58 | 1ኛ | ሕዳር 10/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፡-
- ከላይ የተመለከተውን ንብረት ለመግዛት ፍላጎትና አቅም ያለው የሐራጅ ተሳታፊ የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋ ¼ኛ (25%) የሐራጅ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማቅረብ በሐራጁ ቀን ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት በመመዝገብ መሳተፍ ይችላል።
- ሐራጁ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ይከናወናል።
- ለሐራጅ ማስከበሪያ የሚያዘው ገንዘብ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብለት ሲሆን ሐራጁን ላላሸነፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። የሐራጁ አሸናፊ በራሱ ፈቃድ ሐራጁን ከተወ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሠረዛል።
- የሐራጁ አሸናፊ መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን ቀረጥ ከፍሎ ወይም ከቀረጥ ነጻ መብት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እና የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ 15 በመቶ (15%) ተ.እ.ታ (VAT) እና ሌሎች በሕጉ መሠረት የሚከፈለውን ማናቸውንም ክፍያ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን በመክፈል ስመ-ንብረቱን ወደ ራሱ ማዛወር አለበት።
- የሐራጁ አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ አለበት፤ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖና ጨረታው ተሠርዞ አዲስ የሐራጅ ማስታወቂያ ይወጣል።
- ስለንብረቱ ዝርዝር ሁኔታ እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 057-660-7347 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ማንኛውም በሐራጁ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ንብረቱ በሚገኝበት ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ነቀምቴ ከተማ ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት መርሐ-ግብር መሠረት መጎብኘት ይችላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank, Nekemte District, is auctioning a repossessed Toyota Double Cab vehicle (Model KUN25L-PRMDHV) in Nekemte town, sold as-is for cash under Proclamations 1147/11, 216/92 and 97/90. Bidders must register by presenting a bank-certified CPO for 25% of the reserve price.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
