ገልባጭ የደረቅ ጭነት መኪና እና የሰው እና የደረቅ ጭነት መኪና ሽያጭ ጨረታ (2 ሎት) - በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የተጫራቾች መመሪያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መኪኖች በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ፡-
- ሎት አንድ ፡- ገልባጭ የደረቅ ጭነት መኪና
- ሎት ሁለት ፡- የሰው እና የደረቅ ጭነት መኪና ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት የጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ ማንኛውም ተወዳዳሪ መወደደር እንዲችሉ ፤
- ተጫራቾች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 09/03/2019 ዓ.ም ቀን ድረስ በጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጅዳ ወረዳ አስተዳደር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት የመኪኖቹን ይዘት በማየት የሚወዳደሩበትን የብር መጠን በመሙላት ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች አንድ ኦርጂናል ፡ አንድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለብቻ በማሸግ እነዚህን 3 ዶክመንቶች በአንድ ፖስታ (mother envelope) በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በተጨማሪ እያንዳንዳቸዉ ዶክመንት ላይ ኦርጂናል፤ ኮፒ እንዲሁም CPO በማለት በፖስታው ላይ መጻፍ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ እስከ 10/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዚሁ እለት ማለትም በ10/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ይሁን እንጂ ተወዳዳሪዎች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ህጋዊ የጨረታ ኮሚቴዎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የተወዳደሩበትን ጠቅላላ የብር መጠን 1/4 ለጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ከጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊው ተወዳዳሪ ያሸነፈበትን የብር መጠን ሙሉ በሙሉ በመ/ቤቱ አካውንት ላይ ካስገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ተይዞ የነበረዉ ይመለስለታል።
- ለተሸናፊ ተወዳዳሪዎች አሸናፊው ተወዳዳሪ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ አስይዞ የነበረው ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የሚመለስ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአ/አ ላምበረት መነሀሪያ ጅዳ/ሰርጢ ብለዉ በጣፎ አርባራት መንገድ ተሳፍሮ መምጣት ይችላሉ። ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሰው ስ.ቁ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር፡- 011-673 6328
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Sale of two vehicles by court order in two lots: Lot 1 a tipper/dump truck; Lot 2 a passenger and dry-cargo truck. Bidders must inspect the vehicles in person at the Jida district administration compound and submit bids. Documents in original and copy plus a CPO bid bond, separately sealed in one envelope.
