የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ሥም | የአስያዡ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የቤቱ (የህንፃው) አገልግሎት | ሕንፃው የሚገኝበት አድራሻ - ክልል | ወረዳ | ቀበሌ | የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር | የቦታ ስፋት (በካ.ሜ) | መነሻ ዋጋ (በብር) | ሐራጅ የሚካሄድበት ቀን / ዓ.ም | ሰዓት |
| 1 | አቶ ፍሬገነት ታደለ | ተበዳሪው | ጋፍማ | የመኖሪያ ቤት | ሲዳማ | ቱላ | 01 | 1904/222 | 570 ካ.ሜ | 1,211,733.14 | 08/04/2019 | ጥዋት 4:00-5:00 |
ስለሆነም:-
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ ¼ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈለ ግን ሐራጁ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡ሐራጁም ተሰርዞ ሌላ ሐራጅ ወጥቶበት ሲሸጥ የሐራጁ ሸያጭ ዋጋ ከቀድሞው ሸያጭ ዋጋ የቀነሰ (ዝቅ ያለ ) ከሆነ ልዩነቱንም ጭምር ለመክፈል ይገደዳል፡፡
- ሐራጁ የሚካሄደው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀዋሳ ዲስትሪክት በሚገኘው የሠራተኞች ክበብ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ነው፡፡
- የንብረቱን ሁኔታ በአካል በመገኘት ለማየት ይቻላል፡፡
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሆነ የንብረቱን ስም ዝውውር ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚታወቀው ባንኩ የቀረበውን ዋጋ መቀበሉን ለአሸናፊው በጽሑፍ ሲያረጋግጥለት ብቻ ነው፡፡
- ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
✨ messages.ai_summary
Commercial Bank of Ethiopia, Hawassa District, is auctioning a residential house in Sidama, Tula, on a foreclosure sale. Bidders or legal representatives may participate by depositing 25% of the starting price in cash or CPO. The winner must pay the balance within 15 days. VAT and transfer costs are borne by the buyer.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
