Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ የውርስ መጋዘን ቅጥር ግቢ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125896
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (የማይመለስ፣ በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች (መገናኛ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሪክ፣ መዋቢያ፣ የቤትና ቢሮ፣ ምግብ ነክ፣ የመኪና መለዋወጫ) ሽያጭ ጨረታ (13/2019) - በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- 13/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ - ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት፣ የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ጥራቱን በጠበቀ ስካን በማድረግ ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርበታል።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሰረት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ኦንላይን በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ _ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O ለእያንዳንዱ ኮድ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄዴው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ - ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ጥቅምት 18 ቀን 2019 ጀምሮ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ስለሆነም ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ።
  7. ማንኛዉም ተጫራች የሰጠዉ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታዉ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
    በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (3 ቀናት የሚመለስላቸው ይሆናል።
  9. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በተለጠፈው ፎቶ ብቻ ተመልክተው ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  10. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
  11. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች የሚጭኑት/የሚያቀርቡት ሠነድ ጥራቱን በጠበቀ መሳሪያ ስካን የተደረገ እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ብቻ እንዲያቀርቡ ይመረጣል፡፡
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Aution Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡

ለበለጠ መረጃ፡- የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96 / 046-212-65-95 ይደውሉ፡፡
የቴሌግራም ግሩፕ ፡https://t.me/hawassaawegaged(ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት2018)

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Hawassa Customs Branch invites bids for the sale of abandoned and confiscated goods, including communication equipment, clothing, electrical items, cosmetics, household/office goods, food items, and vehicle/motorcycle parts. Open to individuals and firms with a valid trade license, VAT registration, TIN, and proof of tax payment. Bidding is via the Auction Ethiopia platform. Importers/owners and their families are excluded.
Not stated in the notice: opening date. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender