Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
  • Address አማራ ክልል: ኢትዮጵያ, Phone: 033-4-40-12-30
  • Website
  • Deadline11 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 10,000 (የባንክ ዋስትና ወይም CPO)
  • opening dateበ11ኛው ቀን 3:30
  • Categories Building Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የሕንፃ መሳሪያ እቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጨ-1/0260/2019

የሕንፃ መሳሪያ እቃዎች ግዥ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የሕንፃ መሳሪያ እቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን የመጫኛና የማጓጓዣ ወጪ ሸፍኖ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች ንብረት ማከማቻ መጋዘን ማቅረብ የሚችል፣
  2. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer identificatin number) ያላቸው እና የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  6. የሚገዙትን እቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/በመክፈል የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች ጨረታው በሎት መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) ብቻ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስር ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናውን በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ አንደኛው ቀን 3:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ታሽጎ በ3:30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰአት ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በተመሳሳይ ሰአት በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲሞሉ በነጠላ ዋጋውም ሆነ በጠቅላላ ዋጋው ስርዝ ድልዝ ካደረጉ፣ በጨረታ መክፈቻው ወቅት የተነበበው ዋጋና የተሰራው የሂሳብ ስሌት ከሰላሳ በመቶ በላይ ልዩነት ካለው ወይንም ከሰላሳ በመቶ በታች ልዩነት ኑሮት የሂሳብ ማስተካከያ ካልተቀበሉ ወይንም ከገበያ ጥናቱ እና ከአንድ እስከ ሶስት ከወጡ አሸናፊ ድርጅቶች ከሚወስዱት ዋጋ ሲነጻጸር ተጫራቹ የሞላው ዋጋ ከአስር በመቶ በላይ ከተጋነነ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል።
  12. ተጫራቾች ከገበያ ጥናቱ እና ከአንድ እስከ ሶስት ከወጡ አሸናፊ ድርጅቶች ከሚወስዱት ዋጋ ሲነጻጸር ተጫራቹ የሞላው ዋጋ ከሰላሳ በመቶ በታች የተሰበረ ከሆነ ለእያንዳንዱ የተሰበረ ዋጋ ሁለት በመቶ ከሚያስይዘው የውል ማስከበሪያ በመጨመር የሚያስይዙና የቅድመ ክፍያ የማይጠይቁ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
  13. መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
  14. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 0334401230/0249/0062 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Wag Himra Zone Finance Department invites bids for building materials/equipment for its sector offices, to be delivered to its warehouses. Bidders need a valid trade license, TIN, tax clearance, and VAT registration. The tender is lot-based; specifications are in the bid document.
Save Tender