በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 461 እና 462 የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
[የፍ/ባለመብት እና የፍ/ባለዕዳ ስሞች ከፎቶው በግልጽ አይነበቡም] መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በ25/07/2018 ዓ.ም በተደረገው በእርቅ ስምምነት መሰረት እና በኮ/መ/ቁ/217568 በ30/10/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት 1ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 461 [ስም ከፎቶው አይነበብም] ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በይዞታ ላይ ያረፈበት 30 ካ/ሜ ከጠቅላላ በፐርፖርሽን 63 ካ/ሜ የሚደርሰው ሲሆን በ1988 አርሮ ካርታ (GIS ላይ የሚታይ) ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,437,424 (ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ሃያ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
2ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 462 [ስም ከፎቶው አይነበብም] ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር AA000080304287/1 የተመዘገበ የቤቱ ስፋት 45.08 ካ/ሜ እና የይዞታ ስፋት ጠቅላላ በፐርፖርሽን 154.39 ካ/ሜ ሁለቱም ቤቶች በአንድ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በይዞታ ውስጥ የቀበሌ ቤት ያለበት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,804,462.41 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ አራት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ሁለት ከ41/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ሲ.ሆን፤ እያንዳንዱ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
