Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለመ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114708503
  • Website
  • Deadline03 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100.00 (የማይመለስ፣ online)
  • Bid Securityግልጽ ጨረታ፡ የዋጋው 5%፤ ሐራጅ፡ ብር 100,000 (CPO)
  • opening dateonline (Auction Ethiopia)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የተያዙና የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ በግልጽ ጨረታና ሐራጅ (ቁጥር 16/2019) - በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የተያዙና የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 16/2019

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎችን (ተሽከርካሪዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተለያዩ ዕቃዎች እና ሌሎች) በዕቃ ግልጽ ጨረታ እና በዕቃ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ [የመግቢያው ክፍል ከፎቶው በግልጽ አይነበብም] ከሀሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጫረቱ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም ድረ ገጽ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በመሆኑም

  1. በዕቃ ግልጽና ሀራጅ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ) ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) አንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል።
  2. በጨረታው ላይ የዕቃው ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
  3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በአንላይን አክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMSSON ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በአንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  5. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ/ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፤ ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በአንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች በሚከተሉት የጨረታ ቀናት (ሰሌዳ) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
    ተ.ቁየቅ/ጽ/ቤቱ ስምየጨረታው አይነትየጨረታ ሰነድ መሸጫና ዋጋ ማቅረቢያ ቀንየጨረታው መዝጊያ እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት
    1አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤትየዕቃ ግልጽእስከ 23/02/2019እስከ 24/02/2019 (4:00 ሰዓት) [ከፎቶው በከፊል የማይነበብ]
    2አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤትየዕቃ ሐራጅእስከ 24/02/2019ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ [ከፎቶው በከፊል የማይነበብ]
  7. የጨረታ መክፈቻ ቦታ ሙሉ በሙሉ የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በአንላይን) የሚከናወን ሲሆን ጨረታውን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ የጨረታውን ሂደት በአንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
  8. ያሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት ከተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለፀው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 - 05 -11 -55 -11
አድራሻ፡- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (አክሽን ኢትዮጵያ)
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011 - 470 - 85- 03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንፃ

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Kality Customs Branch invites bids for the sale of seized and confiscated goods (vehicles, electronics, and other items) via open tender and auction. Bidding is online only through the Auction Ethiopia app or www.auction.et. Bidders need a valid trade license, VAT registration, and tax clearance. Former owners and their families may not participate.
Save Tender