የFabric Belt Splicing Hot Vulcanization Kits እና Super Screw Kits ግዥ (2 ሎት፣ ሙሲፋ/09/2019) - ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/09/2019
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት
- ሎት አንድ (1) ፋብሪክ ቤልት ስፕላይሲንግ ሆት ቮልካናይዜሽን ኪትስ (Fabric belt splicing hot Vulcanization kits)
- ሎት ሁለት (2) ፋብሪክ ቤልት ስፕላይሲንግ ሱፐር ስክሩ ኪትስ (Fabric belt splicing super screw kits).
በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018/2019 ዓ.ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት) ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም.ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም.ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
