የፅህፈት መሳሪያ፣ የቢሮ መገልገያ፣ ፅዳት፣ ህትመት፣ ደንብ ልብስ፣ የመኪና ዲኮር፣ ኤሌክትሮኒክስና የፕሪንተር መለዋወጫ ግዥ (8 ሎት) - የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ ማስኬጃዎች ሎት አንድ የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት ሁለት ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ ሎት ሶስት የጽዳት እቃዎች፣ ሎት አራት የህትመት ሥራዎች፣ ሎት አምስት የደንብ ልብስ የአ ደጋና የጤና መጠበቂያ እቃዎች ፣ ሎት ስድስት የመኪና ዲኮር እቃዎች ፣ሎት ሰባት ቋሚ የእቃና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት ስምንት የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ መለዋወጫ እቃዎች በአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ፡፡
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥራችን 1000383805035 በማስገባት እስሊፑን ይዘው የጨረታውን ሰነድ በሥራ ሰዓት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያው ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሠረት ዋናውንና ኮፒውን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀንን ጨምሮ አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ11ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 8፡30 ይከፈታል ፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል ፡፡ በተጨማሪም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ– 011-6-73-43-16 /011-6-73-21-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያለዉ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Lemi Kura Sub-City Small Taxpayers Branch Office seeks suppliers for stationery, office supplies, cleaning materials, printing services, uniforms and health supplies, vehicle decor, fixed assets and electronics, and printer/photocopy spare parts across 8 lots. Bidders must be on the government suppliers list, tax-compliant, and VAT-registered.
