ሲንቄ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
SIINQEE BANK S.C.
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር ሲባ/ህአዳ/ሐራጅ/04/2019
ሲንቄ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪ ቅርንጫፍ | ለጨረታ የቀረበው ንብረት | ከተማ/ክ/ከተማ/ቀበሌ/ወረዳ/የቤት ቁጥር | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | ሰዓት | ጨረታው የሚወጣው |
| 1 | ፍቃዱ እና መስፍን የብረታብረት ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር | ፍቃዱ እና መስፍን የብረታብረት ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር | አዳ | ለመነፋክቸሪንግ አገልግሎት የሚያገለግል መጋዘን | ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ ገላን ቀበሌ | BMG/K/L/I/FM/2013 | 3000 ካ.ሜ | 63,172,717 | 17/2/2019 | 4:30-6:00 | ለ1ኛ ጊዜ |
| ኤች ቢ.ኤም ኮንስትራክሽን እቃዎች አቅራቢ ኃላ/የተ/የግል ማህበር | አዳ | ለመነፋክቸሪንግ አገልግሎት የሚያገለግል መጋዘን | ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ ገላን ቀበሌ | BMG/K/L/I/H-B.M.A/2013 | 3000 ካ.ሜ | 63,991,166.08 | 17/2/2019 | 8:00-9:30 | ለ1ኛ ጊዜ | ||
| 2 | ዳግማዊት ሲሳይ ሉምባሶ | በቀለች ሞገስ ማናግደዉ | ሀርቡ | የጋራ መኖሪያ ቤት | አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ወረዳ 10 (የጋራ መኖሪያ ቤት) | AA00006100 73132670216 | 53.52ካ.ሜ | 2,245,610 | 18/3/2019 | 4:30-6:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
የሐራጁ ደንቦች፣
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚገኘው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጁ ሂደት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ማን እንደሆነ ብቻ የሚገለፅ ሲሆን ጨረታውን ያሸነፈው ሰው/አካል ስለማሸነፉ በሚመለከተው የባንኩ አካል ከተረጋገጠ በኋላ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡
- ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
- ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ ፤ ካዛንቺስ የሚገኘው ሲንቄ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ይሆናል፡፡
- ስለስም ዝውውር የሚከፈል ክፍያ እንዲሁም የሊዝ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍሉ በሕግ የተወሰኑ ከታክስ እና ግብር ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎችን ገዢው/አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ ይከፍላል፡፡
- የንግድ ማህበራትን በመወከል መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ የማህበሩን ህጋዊ ሰውነት ያለዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የመመስረቻ ወይም እና የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ህጋዊ የውክልና ስልጣን ሰነድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለሐራጅ የቀረቡ ንብረቶችን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡
- ተጫራች የጨረታ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰዉ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የሲንቄ ባንክ ህግ አገልግሎት ክፍል ስልክ ቁጥር (+251-11557-6016)፣ ፤ አዳ ቅርንጫፍ (0115571965) እና ሀርቡ ቅርንጫፍ 0115578781 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ሲንቄ ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Siinqee Bank is selling repossessed assets by open auction: two warehouses in Shaggar City (Galan) for manufacturing use, and a shared residential house in Addis Ababa (Bole). Bidders must deposit 25% of the starting price via CPO. Only bidders, debtors, and property pledgers (or legal representatives) may attend.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
