Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
  • Address Bole Road, behind Dembel City Center, Seid Yassin Building., addis ababa,Ethiopia, Phone: 011-1-569992
  • Websitehttps://commercialnominees.com/
  • Deadline10 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineThe Reporter
  • Bid Document Priceብር 100.00
  • Bid Securityብር 100,000 (CPO)
  • opening dateህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም 4:30
  • Categories Water System Installation , Building Construction

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን የሚያስፈልጉ ለሲቪል ስራ፣ ለውሃ ዝርጋታ እንዲሁም ለቆሻሻ ውሃ ማስገጃ ግንባታ ስራ ደረጃ 5 መሳተፍ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/13/19

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን የሚያስፈልጉ ለሲቪል ስራ፣ ለውሃ ዝርጋታ እንዲሁም ለቆሻሻ ውሃ ማስገጃ ግንባታ ስራ ደረጃ 5 መሳተፍ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2:00-6:00 እና ከሠዓት 7:00-11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት 2:00-6:00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ (Commercial Nominees PLC)

✨ messages.ai_summary
Commercial Nominees PLC seeks grade 5 contractors for civil works, water distribution, and wastewater construction. Bidders must submit a renewed business license, eligibility letter, supplier registration proof, VAT certificate, CPO bid bond, and item specifications in sealed envelopes.
Save Tender