የሀዋሳ ከተማ ው/ፍ/አገ/ድርጅት 2017 እስከ 2018 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን የድርጅቱን የ2 ዓመታት የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫ ሪፖርትን በገለልተኛ የኦዲት ድርጅቶች ግልጽ ጨረታ በማጋበዝ የጨረታው አሸናፊ በሚሆነው ድርጅት ኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ፋይናንሽያል ኦዲት ምርመራ አገልግሎት የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግሸ መለያ ቁጥር ግንብ/007/2019
የሀዋሳ ከተማ ው/ፍ/አገ/ድርጅት 2017 እስከ 2018 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን የድርጅቱን የ2 ዓመታት የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫ ሪፖርትን በገለልተኛ የኦዲት ድርጅቶች ግልጽ ጨረታ በማጋበዝ የጨረታው አሸናፊ በሚሆነው ድርጅት ኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ገለልተኛ የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ:-
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ቦርድ የተሰጠ የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የኢትዮጵያ የሂሳብ አዋቂዎችና ኦዲት ቦርድ ባወጣው መስፈርት መሰረት በደረጃ አንድ ላይ ለተጠቀሱ ድርጅቶች የኦዲት ምርመራ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ፡ ፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች በፋይናንስ የኦዲት ምርመራ ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ ያልታገዱ ስለመሆናቸው የሚገልጽ "ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተሰማሩበት የንግድ ዘርፍ ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ በተደነገጉ ማናቸውም ህጎችና ደንቦች መሰረት ህጋዊ ስለመሆናቸው ሊያስረዱ የሚችሉ ከላይ ያልተጠቀሱ ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎች ካላቸው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ በመያዝ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) ብቻ በመክፈል ከድርጅቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ክፍል 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁር 19 በመቅረብ መግባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ20ኛው የስራ ቀን 11:30 ላይ ታሽጎ በ21ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡ ፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ
የሀዋሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በስተደቡብ አዲሱ መናሃሪያ በሚወስደው አስፋልት በ600 ሜትር ርቀት ላይ በስተቀኝ በኩል
ሀዋሳ፤ ኢትዮጵያ
የሀዋሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Hawassa City Water & Sewerage Service Enterprise seeks independent audit firms to audit its financial statements for two consecutive budget years. Eligible bidders must hold a renewed professional license from Ethiopia's Accounting and Auditors Board, be licensed to audit Grade 1 entities, have a valid business license and VAT registration, and provide a TIN certificate.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
