የAir Slide Conveying Media፣ Air Slide Fabric እና Martini Cloth for Pneumatic Conveyor ግዥ (3 ሎት፣ ሙሲፋ/06/2019) - ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/06/2019
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል
- ሎት አንድ(1) ኤር ስላይድ ኮንቬሪንግ ሚዲያ (Air Slide Converying Media)
- ሎት ሁለት(2) ሲሚንት ፕላንት ኤር ስላይድ ፋብሪክ ፎር ኤር ስላይድ ኮንቬር (Cement Plant Air Slide Fabric For Air Slide Conveyor).
- ሎት ሶስት(3) ኤር ስላይድ ኮንቬሪንግ ሚዲያ (ማርቲን ክሎዝ ፎር ኑማቲክ ኮንቬየር) (Air Slide Conveying Media(Martini Cloth for Pneumatic Conveyor).
በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ደፈልጋል፡፡
ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018/2019 ዓ.ም)፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት) ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 % በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም.ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
